በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ ፍስሀ ፀጋዬ የህብረት ስራ ማህበራት ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ መሰረት እንደሚጥሉ አስረድተዋል፡፡ይቻላል የቁጠባ እና ብድር ኃ/ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር የቁጠባ አስፈላጊነትን በመረዳት እና አባላትን በማሳተፍ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ፍስሀ መክረዋል፡፡የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አማካሪው አቶ ፍስሀ ማህበራት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እየሆኑ መምጣቻተውን ገልፀዋል፡፡አክለውም በሂደት እያደጋችሁ ወደ ትልቅ ደረጃ መድረስ ትችላላችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡የወላይታ ሶዶ ከተማ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አየለ ዱጤቦ ይቻላል የቁጠባ እና ብድር ኃ/ የተ/ የህብረት ስራ ማህበር በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ አንዱ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡የወላይታ ሶዶ ከተማ ፈጣን ልማት መሰረቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ነው ያሉት አቶ አየለ መስራት እየቻሉ የመነሻ ገንዘብ ለቸገራቸው ምላሽ የሚሰጥ የሰለጠነ አካሄድ መሆኑን ገልፀዋል።በከተማ ደረጃ 65 መሰረታዊ የቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት መኖራቸውን የተናገሩት አቶ አየለ በህብረት ስራዎች መካከል መተባበር እና መቀናጀትን መፈጠር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ይቻላል የቁጠባ እና ብድር ኃ/ የተ/ የህብረት ስራ ማህበር መስራች እና ዋና ሰብሳቢ አቶ መስፍን መምህሩ በጥቂት አባላት ከአንድ አመት በፊት የተሰመረው ማህበር በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚሊየኖችን የሚቆጠር ካፒታል ማፋራቱን አስታውቀዋል፡፡አባላትን ስለቁጠባ በማስተማር እና ግብአት በሟሟላት ተወዳዳሪ እና መተራጭ የህብረት ስራ ማህበር ሆኖ ለመቀጠል ይሰራል ብለዋል አቶ መስፍን ፡፡ ይቻላል ለቀጣዩ የበጀት አመት የአባላትን ቁጥር ለመጨመር እና የካፒታል መጠኑን ለማደግ ማቀዱንም አቶ መስፍን ገልፀዋል፡፡የይቻላል የቁጠባ እና ብድር ኃ/ የተ/ የህብረት ስራ ማህበር አባላት ባገኙት ብድር አማካይነት ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን በሰጡን አስተያየት ላይ ተናግረዋል፡፡






